የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራር ፣ የኮርፖሬት ልዩ ልዩ ክፍሎችና የኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጆች ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በስልጠናው ላይ የማሰጀመሪያ መልዕክት ያስተላለፉት የኮርፖሬሽኑ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው ለተቋም ለውጥ በሰው አዕምሮ ላይ መስራት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ገልፀዋል።ባለፉት ሁለት አመታት በርካታ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሕይወት ሞሲሳ በስልጠና መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።
በቀጣይም ወደ ገበያው ሊያስገባን የሚችልና ተወዳዳሪነትን ታሳቢ ያደረጉ ምርቶች ላይ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ተውስቷል ።
Total Quality Management በሚል ርዕስ ላይ በኮርፖሬሽኑ ቦርድ ሰብሳቢ ፕ/ር ዳንኤል ቅጣው ስልጠና እየተካሄደ ይገኛል። የኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባል አቶ በዛብህ ገብረየስ ከጥራትና ፓራዳይም ሺፍት ጋር የተያያዘ ውይይት አድርገዋል።