በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፀረ ጾታዊ ጥቃት (ነጭ ሪቫን) ቀን እና የአለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ። በአሉ በኢንዱስትሪዎች ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቶ ነው ዛሬ በማእከል ደረጃ የማጠቃለያ ፕሮግራሙ የተካሄደው፡፡ የዋና መስሪያ ቤት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ከኢንዱስትሪ የተወጣጡ ሰራተኞች በተገኙበት ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።እለቱን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የግሩፑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና ሀብት አሰተዳደር ዘርፍ ሀላፊ አቶ ክፍሌ ገ/ማሪያም ባስተላለፉት መልእክት ብልሹ አሰራርና ሙስናን ለመዋጋትና ለመከላከል የአመራሩ ሚና የላቀ ነው ብለዋል፡፡በመሆኑም ከወረቀት ባለፈ በተግባር የሚታይ ስራ በመስራት ሀላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል ሲሉ ገልፀዋል። መላው አመራርና ሰራተኛ ግሩፑን በሃቀኝነትና በስነ ምግባር በማገልገል ግሩፑ የጀመረውን የለውጥ ጉዞ ከዳር ማድረስ ይገባልም ነው ያሉት፡፡የጸረ ጾታዊ ቀንን በማስመልከትም ባስተላለፉት መልእክት ሴት ልጅ እናት መሆኗን በማስታወስ እናቱን የሚወድ ሁሉ የሴቶችን ጥቃት ሊከላከል ይገባዋል ብለዋል፡፡የግሩፑ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ አገልግሎትና የስነ ምግባርና መልካም አስተዳደር አገልግሎት ሃላፊዎች የመወያያ ጽኁፎችን አቅርበዋል፡፡ሴቶችን በማህበራዊ፣በኢኮኖሚያዊ እና በፖሎቲካዊ ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥ በሁሉም መስክ ሁለንተናዊ ድጋፍ ያስፈልጋል ተብሏል።በግሩፑ ባሉ ሁሉም አሰራሮች ስርአተ ፆታን አካታች በማድረግ የሴቶችን ዉሳኔ ሰጪነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል።የፀረ ጾታዊ ጥቃት (ነጭ ሪቫን) ቀን በአገራችን ለ16ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ ሰላም ይስፈን በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርስ ጠቃት ይቁም በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን፣አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በአገራችን ለ17ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ “በስነ ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።በተጨማሪም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረት ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን ድጋፍ ለማድረግ በዋናዉ መስሪያ ቤትና ከኢንዱስትሪዎች ያሉ ስራተኞችን በማስተባበር የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን የማሰባሰብ ተግባር ተከናውኗል፡፡፡፡በዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይም ከውስጣዊ ችግራችን በበለጠ የውጭ ጫናዎች መበራከትን የሚቃወም የበቃ (NO MORE) መልእክት በማስተላለፍ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡
https://www.facebook.com/eegroup/photos/pcb.1084050282408365/1084050045741722/