ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለሃገር መከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች የ16.5 ሚሊየን ብር የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡በትናንትናው እለት አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በመገኘት ለተፈናቀሉ ወገኖችም ድጋፍ አድርጓል፡፡ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ምርታማነቱን ለማሳደግ የተለያዩ የሪፎርም ስራ ውስጥ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ከዚህ ጎን ለጎንም ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ተሳትፎን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ግሩፑ በትናንትናው እለት አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በመገኘት ለዞኑ መስተዳድር ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በድጋፍ አበክቷል፡ከተበረከቱት ቁሳቁሶች ውስጥ ፍራሾች፣ፍሪጅ፣የተለያዩ የመመገቢያና የማብሰያ ቁሳቁሶች ይገኙበታል፡፡የፕላስቲክ ወንበርና ጠረጴዛዎች በዞኑ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ውድመት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት፣ት/ቤቶችና የተለያዩ ተቋማት ታስበው የተለገሱ ናቸው፡፡እንደ ፓስታና መኮረኒ ያሉ የእለት ደራሽ ምግቦችም በልገሳው የተካተቱ ሲሆኑ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችም በድጋፉ ተበርክተዋል፡፡ ለወገን ደራሽ ወገን ነው እንዲሉ፣ ግሩፑ ከለገሰው በተጨማሪ ከዋናው መ/ቤትና ከኢንዱስትሪዎች ሰራተኞች በመተባበር የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል፡፡ልባሽ ጨርቆች፣የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችና የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ሰራተኛው በመለገስ ለወገን አለኝታነቱን ያረጋገጠበት ነው፡፡እነዚህ አጠቃላይ ቁሳቁሶች 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የሚደርሱ ሲሆን ከሌሎች ጋር ተደምሮ ለተፈናቃዮች የተደረገው ድጋፍ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ደርሷል፡፡እነዚህ በአምስት ሎቤድ መኪና የተጫኑ ተሸካሪዎች ደብረ ብርሃን ከተማ ሲደርሱ የዞኑ መስተዳድር አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገ/ጻዲቅ ኢትዮ ኢንጂነሪን ግሩፕ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጎናችን በመቆሙ ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡ የግሩፑ ሰራተኞች ላደረጉት ተሳትፎም ምስጋናቸውን አቀርበዋል፡፡አሸባሪው የህወት ቡድን በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ሰፊ የህይወትና የንብረት ውድመት ማድረሱን ያስታወሱት ሃላፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር ዳር በመነሳት የወረዳዎቹን ነዋሪዎች ለማደራጀት ሰፊ ተሳትፎ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕም የዚህ አካል በመሆኑ ደስ ይለኛል ብለዋል፡፡ በቀጣይ ከግሩፑ ጋር በሁሉም መስኮች ተባብረው እንደሚሰሩም ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ዜና ግሩፑ ለመከላከያ ሰራዊታችን የተለያዩ ድጋፎችን ያደረገ ሲሆን ድጋፉን በቀጣይ በሁሉም መስኮች አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል እና በአፋር ክልል ወረራ የፈጸመውን አሸባሪውን የህወሃት ቡድን እየደመሰሰ ለሚገኘው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከፍተኛ ኩራትና ክብር ይሰማዋል፡፡ከዚሁ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም አጋርነታችንን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ ድጋፎችን ከዚህ ቀደም ያደረግን ሲሆን አሁንም እያደረግን እንገኛለን፡፡ ለመከመላከያ ሰራዊታችን ያደረግነው ድጋፍ በገንዘብ 13 ሚሊየን ብር በቁሳቁስ 1.1 ሚሊየን በድምሩ 14.1 ሚሊየን ብር ያህል ነው፡፡ሰራተኛው ከደሞዙ ላይ እንዲቆረጥ በወሰነው መሰረት 8 ሚሊየን ብር ድጋፍ እያደረግን እንገኛለን፡፡የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ላስተባበረው መርሃ ግብር 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገናል፡፡በቁሳቁስ ደግሞ ግምታዊ ዋጋቸው 1.1 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የመገልገያ እቃዎችን ድጋፍ እያደረግን እንገኛለን፡፡በተጨማሪም ከባድ ተሸከርካሪዎችንና ባለሙያዎቻችን ግንባር ድረስ በመሄድ እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን፣ቢሾፍቱ የሚገኘውን ገስት ሃውስ ለዚሁ ተግባር የማመቻቸት ተግባር አከናውነናል፡፡2 ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በነገው እለት 3ኛ ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር በዛሬው እለት እያካሄድን እንገኛለን፡፡ግሩፑ በሁለንተናዊ መልኩ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡