በግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት የአለም አቀፉ የሴቶች ቀን ተከበረ፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰራ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ተናገሩ፡፡
በግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት የአለም አቀፉ የሴቶች ቀን ተከብሯል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው አምባሳደር ምስጋኑ በዋናው መስሪያ ቤት የተዘጋጀውን የህጻናት ማቆያ ማእከልንም መርቀው ከፍተዋል፡፡
በበአሉ ላይ ባስተላለፉት መልእክት የህጻናት ማቆያው መከፈት ሴቶች በስራቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉና ሃገር ተረካቢ ጤናማ ህጻናትን ለማሳደግ ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል፡፡
ሴቶች የማህበረሰቡ ግማሽ አካላት መሆናቸውን ያስታወሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው ሃገራዊ ልማትን ለማረጋገጥ ሴቶችን ለማሳተፍ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡
የሴቶች ቀንን ማክበር ግንዛቤን ለማሳደግ የሚረዳ ቢሆንም ሴቶችን ማክበር ፋይዳው የላቀ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
የግሩፑ ሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ አገልግሎት ሃላፊ ወ/ት ሶስና ሳህለማርያም በበኩላቸው በግሩፑ የሴቶችን ተጠቃሚነት ሊያሳድጉ የሚችሉ አሰራሮችና መመሪያዎች መዘርጋታቸውን አስታውሰው ለተፈጻሚነታቸው ሁሉም መስራት አለበት ብለዋል፡፡
በኢንዱስትሪዎች በተለያዩ ስነ ስርአቶች በአሉ መከበሩንም በመገለጽ ጭምር፡፡ሴቶች በሃገር አቀፍ ደረጃ በፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሃላፊነት ውስጥ እንዲሳተፉ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታችና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአሉ በተለያዩ አዝናኝ የኪነጥበብ ስራዎችና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡
በሀገራችን ለ46ኛ ጊዜ “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ”፣እና በአለማችን ለ111 ኛ ጊዜ “የስርአተ ፆታ እኩልነት ማረጋገጥ ለዘለቄታዊ ልማት በሚል መሪ ቃል ” አለም አቀፉ የሴቶች ቀን እየተከበረ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

https://www.facebook.com/eegroup/photos/pcb.1137585430388183/1137585217054871/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *