ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
በፊርማ ስነ ስርአቱ ላይ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ፣የግሩፑ የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ም/ል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ገ/ማርያም፣የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ደርቤ አስፋውና የባንኩ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል፡፡
በባንኩ ዋና መ/ቤት የተካሄደውን የፊርማ ስነ ስርአት ግሩፑን ወክለው የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ እና ባንኩን በመወከል ፕሬዝዳንቱ አቶ ደርቤ አስፋው ፈርመዋል፡፡
በዚሁ ወቅት የባንኩ ፕሬዝዳንት እዚህ ስምምነት ላይ ለመድረስ ያላሰለሰ ጥረት መደረጉን አስታውሰው በቀጣይ በጋራ መስራት እንጀምራለን ብለዋል፡፡
ባንኩ በዘረጋቸው ፓኬጆች መሰረት በጋራ ለመስራት እንደሚፈልጉም ጠቅሰዋል፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በበኩላቸው በጋራ ተጠቃሚነት መርህ እንደሚሰሩና ይህ ለሁለቱም ተቋማት እድል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ባንኩ በጥቂት አመታት ውስጥ ተወዳዳሪ ለመሆን መቻሉን አስታውሰውም በግሩፑ ያለውን እምቅ ሃብት በማውጣት ባንኩንም ግሩፑንም ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ ለግሩፑ የብድር አቅርቦትን፣የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን፣ እንዲሁም የሰራተኛ የቤኔፊት ፓኬጆችንና ሌሎች ማእቀፎችንም ያካተተ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *