ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች የተካተቱበት ቡድን በአቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዱስትሪ ጉብኝት አደረገ።

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ በሃገሪቱ የብረት ዘርፍ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተናገሩ፡፡
በዛሬው እለት ዋና ስራ አስፈጻሚው እና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች የተካተቱበት ቡድን በኢንዱስትሪው ጉብኝት አድርጓል፡፡
የኢንዱስትሪው የስራ እንቅስቃሴና የፋብሪካዎች እንቅስቃሴ የተጎበኘ ሲሆን ውይይትም ተካሂዷል፡፡
ኢንዱስትሪው ለስኳር፣ ለሲሚንቶ ፋብሪካዎችና ለተለያዩ ፋብሪካዎች መለዋወጫዎችን በማቅረብ ይታወቃል፡፡የሃይል ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ፋብሪካዎችና ተቋማት የተለያዩ መለዋወጫዎችንም ያቀርባል፡፡
እነዚህን መለዋወጫዎች በማምረት በሃገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የበኩሉን ሚና ለመወጣት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተመላክቷል፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እንደተናገሩት ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪ ለማድረግ ግሩፑ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
እንደ ሃገር ከፍተኛ ተልእኮን የተቀበለ ኢንዱስትሪ መሆኑንም በማንሳት የተቀበለውን ተልእኮ ማሳከት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
የሰው ሃብቱ አቅም ያለውና ተወዳዳሪ እንዲሆን፣ ኢንዱስትሪው በቴክኖሎጂ እንዲዘምን ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በአጭር ጊዜ መከናወን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
አሁን በኢንዱስትሪው የተጀመረውና ውጤት እየታየበት ያለውን ምቹ የስራ አከባቢን ለመፍጠር እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ ላይም ምክክረ ተካሂዷል፡፡
ተከታታተይ የሆነ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በማከናወን፣የስልጠና መርሃ ግብሮችን በመፈጸም ጠንካራ የስራ ባህል ለመገንባት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴም ሊጠናከር ይገባል የተባለ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የዋና መ/ቤት የስራ ላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *