ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም (ኢኢግ) በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግራንድ አፍሪካ የሽልማት ድርጅት የተዘጋጀውን ሽልማት ተቀበለ፡፡
የ20ኛ ዙር የግራንድ አፍሪካ የሽልማት ድርጅት የተቋማትና የአመራርነት ሽልማት መርሃ ግብር ላይ ኢንዱስትሪው የፕላቲንየም ደረጃ የዋንጫ እና የሜዳሊያ እንዲሁም የመካከለኛ አመራሮች የዲፕሎማ ሽልማት ተቀብሏል፡፡
ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በሽልማት ድርጅቱ በተደረገ ጥልቅ ምዘና የተመዘነ ሲሆን በተደረገው የተቋምና የአመራርነት የምዘና ልኬት ተግባር ከፍተኛ ዉጤት በማምጣቱ ተሸላሚ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅና የኢንዱስትሪው አመራሮች በጋራ በመሆን ከቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እጅ ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡
የሽልማት ድርጅቱ በዋናነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአምራችነት እና በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ፣ ለሀገርና ለወገን የሚጠቅሙ ስራዎችን የሰሩ ተቋማትንና መሪዎችን የሚያበረታታ ነው።







