ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው ሃገር አቀፍ የኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ሲምፖዚየምና ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው ሃገር አቀፍ የኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ሲምፖዚየምና ኢግዚብሽን ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡
በተለያዩ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላት፣ የዩኒቨርስቲው ተመራቂ ተማሪዎችንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በፕሮግራሙ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የዩኒቨርስቲው የምርምርና የማህረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ገዛህኝ ደግፌ እንዳሉት ኢንዱስትሪዎችና ዩኒቨርስቲዎች ተቀራርበው በመስራት የሃገሪቱን የምርታማነት ክፍተት መሙላት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡
ደብረ ብርሃን አከባቢ ላሉትና በመላ ሃገሪቱ ለሚገኙት ኢንዱስትሪዎች የምርምር ስራዎችን በጋራ በመስራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የበኩላችንን እንሰራለን ብለዋል፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸው የኢንደስትሪያል ኢንጂነሪንግ ሙያ በሃገሪቱ ለሚስተዋሉት የኢንዱስትሪ ምርቶች ጥራትና ምርታማነት ጉድለት ለመሙላት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ ሙያዊ ሃላፊነታችንን ለመወጣት መስራት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል፡፡
ሃገሪቱ ወደ ኢንዱስትሪ ለምታደርገው ጉዞና ኢንዱስትሪው ለሃገሪቱ አድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ብዙ መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በስሩ ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ያስታወሱት ሃላፊው እንደ ደብረ ብርሃን ካሉ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ተቀራርቦ በመስራት ግሩፑን ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስሩን በማጠናከር ሁለቱም አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል በጋራ መስራት አለብን ብለዋል፡፡
ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ጋርም በስልጠና፣ በኢንተርን ሺፕ፣በአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች በጋራ እንደሚሰሩም በማስታወስ፡፡
የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አስናቀ ጉዲሳ በበኩላቸው የካይዘን ፍልስፍና በጃፓኖች ለውጥ ሊያመጣ የቻለው የጃፓን ዩኒቨርስቲዎች ባበረከቱት አስተዋጽኦ ጭምር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የኢንስትሪያል ኢንጂነሪንግን ሙያ በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያመጣ ተጋግዘን እንሰራለን ብለዋል፡፡
ከሲምፖዚሙ በተጨማሪ ኢግዚብሽን የሚካሄድ ሲሆን ኢግዚብሽኑ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናትም ይቀጥላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *