ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለዋና መስሪያ ቤቱ ህንጻ ሪኖቬሽን ስራ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን እና ሱፐርቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር ኮንትራት ተፈራረመ፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለዋና መስሪያ ቤቱ ህንጻ ሪኖቬሽን ስራ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን እና ሱፐርቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር ኮንትራት ተፈራረመ፡፡
ግሩፑ መሃል ሜክሲኮ ላይ የሚገኘውን ዋና መስሪያ ቤቱን ነው ሪኖቬት እያስደረገ የሚገኘው፡፡
ስራው ባለ 5 ፎቅ፣ ባለ 1 ፎቅና ግራውንድ ላይ የሚገኙ ህንጻዎችን ያካተተ ሲሆን በ7 ወራት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው፡፡
የግሩፑን ሎጎዎች እና ምልክቶች ታሳቢ ያደረገ ዙሪያ አጥር፣ ህንጻዎቹን የሚያገናኙ ተንጠልጣይ ድልድዮች እና የግሪነሪ ስራዎች በስምምነቱ ውስጥ የተካተቱ ናቸው፡፡
በዘመናዊ ፈርኒቸሮች የተዋቡ ቢሮዎች፣መሰብሰቢያ አዳራሾች ፣ሾው ሩምና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጡ ክፍሎችም ተካተውበታል፡፡
የኮንትራት ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን እና ሱፐርቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን – ኮንስትራክሽን ዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሮቤል ጸጋዬ (ኢንጂነር) ናቸው፡፡
በስምምነቱ ወቅት አምባሳደር ሱሌይማን የኮንትራት ስራው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ግሩፑ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሮቤል ጸጋዬ (ኢንጂነር) በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ልምድ ያላቸው የዲዛይንና የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች በመኖራቸው በተሻለ ጥራት በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *