በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአረንጓዴ አሻራ መክፈቻ መርሃግብር በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ተካሄደ።
ቢሾፍቱ፣ሐምሌ 4፣2015(ኢኢግ)
ሐምሌ 10 ቀን በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እንደ ሀገር ለተያዘው እቅድ ተሳታፊ ለመሆን በግሩፕ ደረጃ የመክፈቻ ፕሮግራም በዛሬው እለት ተካሂዷል።
ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ቃል የሚተገበር ነው።
ኢንዱስትሪው በያዝነው ወር 25 ሺህ ችግኞችን ለመትከል እየተቀሳቀሰ ሲሆን በዛሬው እለት 7 ሺህ የፍራፍሬ ችግኞችን ጨምሮ ለጥላና ለአካባቢ ውበት አገልግሎት የሚውሉ ችግኞች ተተክለዋል።
በመርሃ ግብሩ የተገኙት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የስርአት ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ይርጋ አረንጓዴ አሻራ ስናሳርፍ ችግኝ ብቻ ሳይሆን ፍቅርንና አንድነትንም እተክላለን ያሉ ሲሆን የአየር ብክለት ለመከላከል ብሎም የምንተነፍሰውን ንፁህ አየር ለማግኘት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ አቶ መሃመድ ጀማል ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪቃል እንደ ግሩፑ በመሳተፍ ለሀገር ልማት አሻራችንን ማሰረፍችን የደን ልማትን ከማስጠበቅና የዝናብ ዕጥረትን ለማስቀረት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
የኢንዱስትሪው ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን መንግስቱ የመትከል ስነ ስርአቱ በኢንዱስትሪው ግቢ ውስጥ የተለየ ቦታ ተሰጥቶት የተተከለ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተከልናቸው ችግኞች ለመጭው ትውልድ የሚተላለፍ በመሆኑ ሁሉም አካል ችግኞቹን መንከባከብና እንዲፀድቁ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፤አክለውም በሚገኘው የምርት ፍሬ የኢንዱስትሪው ሰራተኞችን እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በመርሃግብሩ የኢንዱስትው ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት እና የግሩፑ ማኔጅመንት አባላትን ጨምሮ የኢንዱስትሪው ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል።


