በኢትዮ ኢንጂነሪግ ግሩፕ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተካሄደ።

ሐምሌ/10/2015 ዓ.ም (ኢኢግ)
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋናው መስሪያ ቤት፣ኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣አዲስማሽን መለዋወጫና ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና ኢትዮ ፕላስቲክ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በጋራ በመሆን በዛሬው እለት ችግኝ የመትከል መርሃግብር አካሂደዋል።
ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር “ነገን ዛሬ እንትከል “በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበረ ይገኛል።
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ይህ ቀን ሀገራችንን ብቻ ሳይሆን አለምን የማዳን አሻራ የምናሳርፍበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ተፈጥሮንና አካባቢያችንን ባለመንከባከባችን ለድርቅ ተጋልጠናል፤ ያሉት አምባሳደሩ ለዚህም አረንጓዴ አሻራችንን እናስቀጥላለን ብለዋል፤ ዘመቻውንም “የህልውና ዘመቻ” ሲሉ ገልፀውታል።
የኤሌክትሮኒክስ ኢክፑመን ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድወሰን ፊሊሞን በመልዕክታቸው የአረንጓዴ አሻራው በኢንዱስትሪው ግቢ ውስጥ የተመረጠ ቦታ ተሰጥቶት የተተከለ መሆኑን ጠቅሰው፤ከመትከሉ ባሻገር መፅደቁን ለማረጋገጥ መንከባከብ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በመርሃግብሩ የግሩፑ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ጨምሮ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት ተሳትፈዋል።
አረንጓዴ አሻራ መርሃግብሩ በቀሩት ኢንዱስትሪዎች እየተካሄ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *