ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዘመናዊ አውቶብሶችን ለማምረት ከቻይናው ዞንግቶንግ ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎና ከዞንግ ቶንግ ኩባንያ ዋንግ ሃቢን ናቸው፡፡
በስምምነቱ ወቅት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እንዳሉት አዲስ ቴክኖሎጂን ወደ ሃገራችን በማምጣት ዘመናዊ አውቶብሶች እንዲመረቱ የምንሰራ ሲሆን በቀጣይ በሀገሪቱ አውቶብሶችን ሙሉ በሙሉ ለማምረት ያለንን እቅድ ለማሳካት የሚያስችሉ ስምምነቶችን ከኩባንያው ጋር እናደርጋለን ብለዋል፡፡
የዮንግ ቶንግ ኩባንያ ተወካይ ዋንግ ሃቢን በበኩላቸው ከኢትዮ ኢንጂነሪን ግሩፕ ጋር በዲዝልና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶች እንዲመረቱ ፍላጎት አለን ብለዋል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከተለያዩ የውጭ ሃገራት ኩባንያዎች ጋር ስምምነት በመመስረት ግሩፑን ወደ ዘመናው የማኑፋክቸሪንግ ተቋም ለመለወጥ እየሰራ ይገኛል::

